ፓስፖርት

የቀድሞው ፓስፖርት ከ November, 24 / 2015 በፊት ከአገልግሎት ውጪ ይሆናል ለተጨማሪ ማብራሪያ እዚህ ይጫኑ

ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል ወደ ውጭ ሲወጡ የተጠቀሙበትን ኦሪጅናል ፓስፖርት ወይም ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ካልቻሉ በልደት የምስክር ወረቀት ብቻ ልናስተናግድ የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ ይህ ወላጆቻቸው ኢትዮጵያዊ ሆነው በውጪ ሀገር የተወለዱ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ሚጠይቁ ህፃናትን አይመለከትም፡፡

 

1.1 አገልግሎቱ ያለቀበት ማንዋል   ፓስፖርት ለመቀየር  መሟላት የሚገባቸውመስፈርቶች

 • ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ኦሪጅናል ፓስፖርት ማቅረብ
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት
 • ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለትኮፒ ማቅረብ
 • ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ
 • የቀኝ እና የግራ የቀኝ አመልካች ጣቶች በተዘጋጀው ፎርም ላይ የጣት አሻራ ማቅረብ::
 • 4 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት)
 • የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል
 • በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት::
 • የአገልግሎት ክፍያ€54.00 መፈፀም
 • በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት ያላቸውአገልግሎት ጠያቂዎች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራ በኤምባሲው ቆንስላክፍል ይሰጣሉ

1.2 አገልግሎቱ ያለቀበት ኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት ለመቀየር  መሟላት የሚገባቸውመስፈርቶች

 • ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገውን ኦሪጅናል ፓስፖርት ማቅረብ
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት
 • ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለትኮፒ ማቅረብ
 • ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ
 • 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለ)ማቅረብ
 • የአገልግሎት ክፍያ€54.00  መፈፀም
 • እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ‘የፓስፖርት አገልግሎቱ የሚሰጠው በፖስታቤት በኩል ስለሆነ አድራሻዎ የተፃፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ’
 • ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው

1.3 ኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት በጠፋ ምትክ ሲጠየቅ

 • የጠፋው ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ሲቀርብ ወይም የጠፋው ፓስፖርት ቁጥር ሲታወቅ
 • ፓስፖርቱ ስለመጥፋቱ በፖሊስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ አያይዘው ሲያቀርቡ
 • 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት)
 • ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ
 • 2 የፓስፖርት መጠየቂያ ማመልከቻ ቅፅ ሞልተው ሲያቀርቡ/ ሲልኩ
 • የፓስፖርት አገልግሎቱ የሚሰጠው በፖስታቤት በኩል ስለሆነ አድራሻዎ የተፃፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
 • ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው
 • አገልግሎትክፍያ:-
  • ለመጀመሪያ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50 %  (81.00 €)
  • ለሁለተኛ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 100 % (108 €)
  • ለሶስተኛ ጊዜ ምትክ በ5 አመት ጊዜ ውስጥ ጥያቄ ከቀረበ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 200 % (162 €)
  • በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት የጠፋባቸው አገልግሎትጠያቂዎችበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራበኤምባሲውቆንስላክፍልይሰጣሉ
  • የፓስፖርትአገልግሎቱየሚሰጠው በፖስታቤት በኩልስለሆነ አድራሻዎየተፃፈበትመመለሻፖስታከነቴምብሩአብሮመላክ

1.4 በጠፋ  ማንዋል ፓስፓርት ምትክ  ሲጠየቅ መሟላትየሚገባቸውመስፈርቶች

 • የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትንማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ  ፎቶ ኮፒ ማቅረብ
 • የፓስፓርቱን ፎቶኮፒ ማግኘት ካለተቻለ የቤተሰብ ሙሉ አድራሻ እና ቤተሰቦች ከሚኖሩበት ቀበሌ ኢትዮጵያዊነትዎን የሚያረጋግጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ካርድ ማቅረብ
 • ፓስፖርቱ ለመጥፋቱ በፖሊስ የተመዘገቡበት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
 • የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት
 • 4 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት) ተያይዞ ሲቀርብ
 • ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ
 • የቀኝ እና የግራ አመልካች ጣቶች በተዘጋጀው ፎርም ላይ መስጠት/መላክ   የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል
 • በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎ  የተረጋገጥ  መሆን አለበት
 • በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት የጠፋባቸው አገልግሎት ጠያቂዎች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራ በኤምባሲው ቆንስላክፍል ይሰጣሉ
 • ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው
 • የአገልግሎት ክፍያ :-
  • ለመጀመሪያ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50 % (81.00 €)
  • ለሁለተኛ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 100 % (104 €)
  • ለሶስተኛ ጊዜ ምትክ በ5 አመት ጊዜ ውስጥ ጥያቄ ከቀረበ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 200 % (162 €)

ለተለያዩ የፓስፖርት አይነቶች ያሉትን የክፍያ ተመኖች ለማወቅ እዚህ ይጫኑ፡፡ የተዘረዘሩት ዋጋዎች በ አሜሪካን ዶላር ሲሆን ትክክለኛ የዩሮ መጠኑን ለማወቅ ቆንስላ ክፍል በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡

ማሳሰቢያ

 • ለኤምባሲው የቆንስላ ክፍል የሚቀርብ አገልግሎት በፖስታ ቤት ከሆነ የባለ ጉዳዩን ሙሉ አድራሻ   የተጻፈበት የአደራ መልእክት (ሬኮማንዴ )መመለሻ  የ6  ዩሮ  ቴምብር አብሮ/ለጥፎ  መላክ::
 • በስፔይን እና ፖርቱጋልየሚኖሩ አገልግሎት ፈላጊዎች ፓስፓርታቸውን ሲልኩ ለመመለሻ የሚሆን በቁጥር 9 ኢንተርናሽናል ኩፖንና ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
 • ለልጆቻቸው ፓስፖርት የሚይቁ ወላጆች በጽሁፍ ማመልከቻ ፣  የወላጅ ፓሰፖርት ና የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ እንዲሁም የልጆቹ የልደት ካርድ ተያይዞ መቅረብ አለበት
 • በትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎች ፓስፖርት ለማሳደሰም ሆነ አዲስ ሲያወጡ የሚማሩበትን ተቋም መተወቂያ አያይዘው ሲያቀርቡ የግኛማሽ ክፍያ ተጠቃሚይሆናሉ

 

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b1%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5/%e1%8b%a8%e1%8d%93%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *