ውክልና መስጠት

የውክልና ሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት
እባክዎ አ ገልግሎቱን ለማግኘት መመሪያውን በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊዎቹን ማስረጃዎች ከነፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡
ሀ/ ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ከሆኑ ወይም  የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካለዎት

  • ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል ልከው ማስፈፀም የሚፈልጉ ውክልናውን በእንግሊዘኛና በሚኖሩበት አገር ኦፊሻል ቋንቋ አስተርጉመው ኖተራይዝ ካስደረጉ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማረጋገጥ ማቅረብ/መላክ ያስፈልጋል፡፡
  • ውክልናውን በፖስታ ቤት ተልኮ የሚፈፀም ከሆነ  የውክልና ሰነዱንና  አድራሻዎ የተጻፈበት የመመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ በማዘጋጀት አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡
  • የመላኪያም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
  • ጉዳይዎ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ከፈለጉ ኤምባሲው ከተረከበበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ፡፡

ለ/ የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ (አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው)

  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል በመላክ የሚያስፈጽሙ ከሆነ የመላኪያም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

ውክልና የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት በተገልጋዮች መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

ሀ/ የአትዮጵያ ዜግነት ላላቸው

   • ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)
   •  አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ
   •  በሚኖሩበት አገር ያሉበትን ሁኔታ (status) የሚያሳይ ማስረጃ  ኮፒ
    • የመኖሪያ ፈቃድ  ወይም
    • የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የተሠጠ የቀጠሮ ወረቀት ወይም
    • ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ
    • ወይምጊዜው ያላበቃ የመግቢያ ቪዛ
   •  የአገልግሎት ክፍያ 57 ዩሮ  ሲሆን፣ ክፍያው ለኤምባሲው በተፃፈ
 • የሐዋላ ክፍያ  /MONDANT CASH/ ወይም
 •  ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ መፈፀም ይቻላል፡፡
 • ውክልናውን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያውን  በጥሬ ገንዘብ መፈፀም ይቻላል፡፡ ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ለ. የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ለያዙ

 • ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)
 • የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ
 • የአገልግሎት ክፍያ 57 ዩሮ  (በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው) ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚኖርበት ሆኖ ክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በፓሪስ የተፃፈ
 •  የሐዋላ ክፍያ /MONDANT CASH/ ወይም
 •  ካሽየር ቼክ /Cashier Check/  መፈፀም ይቻላል፡፡
 • ውክልናውን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያውን  በጥሬ ገንዘብ መፈፀም ይቻላል፡፡ ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ  (አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም   በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው)

 1. አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ኮፒ
 2. የአገልግሎት ክፍያ 87 ዩሮ  (በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው) ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚኖርበት ሆኖ ክፍያው ለኢትዮጵያ ለኤምባሲ በፓሪስ የተፃፈ
 • የክፍያ ትዕዛዝ  /MONDANT CASH/ ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b1%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5/%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%8a%93-%e1%88%b0%e1%8a%90%e1%8b%b5-%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8c%a5-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *