የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ

1 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጠው ያመለከተ የኢትዮጵያ ተወላጅ  የሆነ የውጭ አገር ዜጋ

 • መታወቂያን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደበት አገር የተሰጠው አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ማቅረብ
 • የአመልካቹ አግባብ ካለው አካል የተረጋገጠ የልደት ምስክርወረቀት  ወረቀት ዋናውን ከሁለት ቅጂዎች  ወይም
 • የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት  ቅጂ ዋናውን ከሁለት ቅጂዎች ጋር ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ኢትዮጵያዊያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ (biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነተ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ወይም
 • ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ  በኢትዮጵያዊያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ  ኢትዮጵያዊ አንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ወይም
 • ስልጣን ካለው ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰነድ ማስረጃ ወይም
 • ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨበጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ
 • 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው  ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ
 • አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል
 • በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ትውልድ  ኢትዮጵያውያን ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 5 በመጠቀም በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት::
 • ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 1 በሁለት ኮፒ መሙላት
 • የአገልግሎት ክፍያ 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም
 • አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁት አገልጋዮች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ለማውጣት የአገልግሎት የክፍያ ዝርዝር ለማወቅ እዚህ ይጫኑ

2. አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች ስለሚሰጥ አገልግሎት

 • የልጁ/የልጅቷ ፓስፖርት ቢያንስ ለስድስት ወራት አገልግሎቱ የፀና ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር
 • የልጁን/የልጅቷን የተረጋገጠና ህጋዊ የልደት ምስክር ወቀት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር
 • የወላጁ/የወላጇ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር
 • ልጁ/ልጅቷ ከማመልከቻ ቅፅ ጋር በማያያዝ ከ6ወር ወዲህ የተነሳው/የተነሳችው 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው  ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ
 • ከላይ የተጠቀሱትን ካሟሉ በኋላ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አገልግሎት ክፍያውን 20 የአሜሪካን ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ፈፅሞ መታወቂያው እንዲሰጥለት በወላጅ ጥያቄው ሲቀርብ ሊሰጠው ይችላል
 • ዕድሜ 14 ዓመትና ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆችና 18 ዓመት ያልሞላቸው የጣት አሻራ መስጠት ይጠበቅባቸዋል
 • የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሲደርስ በራሳቸው ጠያቂነት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ  መስፈርትን ሲያሟሉ የተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጣቸው ይደረጋል
 • ማንዋልየትውልድኢትዮጵያ ለማደስወደኢምባሲውበአካልቀርበውለሚጠይቁተገልጋዮችበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራበኤምባሲውበቆንስላክፍልይሰጣል
 • የአገልጎሎት ክፍያ፡-
  • ከ 18 አመት በታች ለሆኑ 20 የአሜሪካን ዶላር በእለቱ ዋጋ ወደ ይሮ ተቀይሮ

3. የኢትዮጵያ ተወላጅ የትዳር ጓደኛ ስለሚሰጥ የኢትዮጵያ ተወላጅነት     መታወቂያ

 • የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ያለው/ያላት የውጭ አገር ዜጋ ለትዳር ጓደኛው/ጓደኛዋ የአትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጥለት/ እንዲሰጥላት ከፈለገ/ች
 • መታወቂያውን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደችበት/ ከወሰደበት አገር የተሰጣትን/የተሰጠውን አገልግሎቱ ቢያንስ ለስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ዋናውንና ከሁለት ቅጅ ጋር
 • መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙበት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያየዞ ሲቀርብና የጋብቻ ሰነዱ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞና በፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ሲቀርብ
 • የትዳር ጓደኛው/ዋ  ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሳውን/የተነሳችውን 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ
 • ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ  2 በሁለት ኮፒ መሙላት
 • የአገልግሎት ክፍያ 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም
 • የእጅ አሻራ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 5 በመጠቀምስጠት፡
  •  አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል
  • በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ትውልድ  ኢትዮጵያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት ::
  • አገልግሎትለማግኘትወደኢምባሲውበአካልቀርበውከመጠየቃቸው በፊትበቅድሚያ ቀጠሮ በስልክ አስይዘው አሻራበኤምባሲውበቆንስላክፍልይሰጣል
 • መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ ፀንቶ ስለመኖሩ በማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
 • የአገልግሎት ክፍያ ፡-
  • 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም
  • አገልግሎት ለማግኘት ወደኢምባሲው በአካል ቀርበው ከመጠየቃቸው በፊት በቅድሚያ ቀጠሮ በስልክ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

 4. የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ  እድሳት

 • ዜግነት ካገኘበት ሀገር የተሰጠውና ቢያንስ ለስድስት ወር አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር
 • ቀደም ሲል የተሰጠው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር
 • የአገልግሎት ክፍያ 200 አሜሪካን ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም፣እንዲሁም መታወቂያውን በወቅቱ ያላሳደሱ በየቀኑ የሚከፈለውን መቀጮ  መክፈላቸው ሲረጋገጥ
 • በጋብቻ ምክንያት  የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት ቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ
 • የትዳር ጓደኛው/ዋ  ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሳውን/የተነሳችውን 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ
 • ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 3 በሁለት ኮፒ መሙላት
 • የአገልግሎት ክፍያ፡-
  • 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

5. የጠፋ ወይም የተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ስለመተካት

 • ለጠፋ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሊሰጠው የሚችለው መታወቂው ስለመጥፋቱ ከአካባቢው ፖሊስ ወይም አግባብ ካለው አካል በቂ የሆነ ማስረጃ ሲቀርብና የጠፋው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ዝርዝር ለኢሚግሬሽን ሲተላለፍ ነው
 • የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲተካ ጥያቄ ያቀረበው በመጀመሪያ መታወቂውን ከሰጠው አካል ውጭ ከሆነ ጥያቄው የቀረበለት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ወይም ኢሚግሬሽን የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ መጀመሪያ የሰጠውን አካል እንደአስፈላጊነቱ መረጃና በጥያቄው ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅ ይኖርበታል፡
 • ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 4 በሁለት ኮፒ መሙላት
 • አመልካች የአገልግሎት ክፍያ 200 የአሜሪካን ዶላር እና ለመጀመሪያ ጊዜ ምትክ ሲሰጥ በመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50% በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም
 • አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ከመጠየቃቸው በፊትበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው ቆንስላ ክፍል ይሰጣል
 • የትውልድ ኢትዮጵያ ለማደስ ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁገት አገልጋዮች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

 

 

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b1%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%8d%e1%8b%b5-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8d%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%89%b3%e1%8b%88%e1%89%82%e1%8b%ab

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *