ቪዛ

ቪዛን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃዎች

 • የቪዛ መጠየቂያ ማመልከቻ የሚገባው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ 3ሰአት – 6ሰአት ከ45  ብቻ ሲሆን
  ቪዛዎትን የመውሰጂያ ሰአት ደግሞ ከሰኞ እስከ አርብ ከሰአት በኋላ ከ9ሰአት እስከ 10ሰአት ከ45 ብቻ ነው፡፡
 • ቪዛ የሚጸናው ከተጠሰጠበቀት ቀን ጀምሮ ነው ፡፡ ሰለዚሆነም የቪዛ ማመልከቻዎን በመላላክ (በፖስታ) የሚጠይቁ ከሆነ በቂ ጊዜ እንዲኖሮት የ 3 ወር ቪዛ እንዲጠይቁ ይመከራል፡፡ የፈረንሳይ ፣ የስፔይን እና የፓርቹጋል ፓስፖርት ያላቸው አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ  የቱሪስት ቪዛ  መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
 • የትውልድ ኤርትራውያን የቪዛ ጠያቂዎች በአካል ኤምባሲያችን ድረስ በመምጣት የቪዛ መጠየቂያ ፎርም መውሰድ ይችላሉ ፡፡

ዲፕሎማቲክ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • ቀኑ ያላለፈበት ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ
 • የቪዛ መጠየቂያ ፎርም ተሞልቶ ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ
 • ከጠያቂው አገር ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ወይም ከሚሰሩበት አለም አቀፍ ድርጅት ኖት ቨርባል ተያይዞ ሲቀርብ
 • የዲፕሎማት ቪዛ የተሰጠው ዲፕሎማት ቤተሰብ አባላትም የዲፕሎማቲክ ቪዛ ይሰጣቸዋል
 • ዲፕሎማቲክ ቪዛ ከክፍያ ነፃ ነው
 • ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ
 • የዲፕሎማቲክ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

ሰርቪስ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • ቀኑ ያላለፈበት ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ
 • የቪዛ መጠየቂያ ፎርም ተሞልቶ ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ
 • ከጠያቂው አገር ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ወይም ከሚሰሩበት አለም አቀፍ ድርጅት ኖት ቨርባል ተያይዞ ሲቀርብ
 • የሰርቪስ  ቪዛ የተሰጠው ግለሰብ ቤተሰብ አባላትም የሰርቪስ  ቪዛ ይሰጣቸዋል
 • የሰርቪስ ቪዛ ከክፍያ ነፃ ነው
 • ፎቶ ግራፍ ያለበትየፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ
 • የሰርቪስ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

የቱሪስት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • ቪዛ መጠየቂያ ፎርም ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ
 • ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ
 • የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ
 • በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ
 • ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅ ኮፒ ተያይዞ ሲላክ
 • የቱሪስት ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

ለትውልድ ኤርትራውያን 

 • የትውልድ ኤርትራውያን የቪዛ ጠያቂዎች በአካል ኤምባሲያችን ድረስ በመምጣት የቪዛ መጠየቂያ ፎርም መውሰድ ይችላሉ ፡፡
የቱሪስት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር
ፈረንሳይ ሲጠየቅ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠየቅ
አንድ ጊዜ መግቢያ 1 ወር 36€ ለአንድ ጊዜ መግቢያ 1 ወር 45€
3 ወር 54€ 3 ወር 63€
ለብዙ ጊዜ መግቢያ 3 ወር 63€ ለብዙ ጊዜ መግቢያ 3 ወር 72€
የትራንዚት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር
ለ 12 ሰአት 21.50€
ለ 24 ሰአት 36.00€
ለ 48 ሰአት 45.00€
ለ 72 ሰአት 54.00

 

የሥራ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • የሥራ  ቪዛ በአመልካቹ ወይም በወኪሉ አማካኝነት የመጠቂያ ፎርም ተሞልቶ  ከአንድ ጉርድ  ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ
 • አመልካቹ ወደ ኢትዮጵያ ለስራ የሚሄዱበትን ምክንያት ሊያስረዳ የሚችል  ደብዳቤ ማቅረብ ሲችሉ
 • አመልካቹን ኢትዮጵያ የሚጋብዘው ድርጅት አዲስ አበባ ኢሚግሬሽን ቀርቦ ለአመልካች የስራ ቪዛ ፈቃድ ጠይቆ ሲያገኝ
 • ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ
 • የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ
 • በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ
 • ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ
 • የስራ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

የስራ ቪዛ የዋጋ ዝርዝር

የቪዛ አይነት የቪዛው መጠሪያ              የቪዛው ዋጋ
ለአንድ ጊዜ እስከ 1 ወር ለለአንድ ጊዜ እስከ 3 ወር ብዙ ጊዜ እስከ 3 ወር
ለኢንቨስትመንት / ለንግድ ስራ/ I-V           27.00€    36.00 €
ለተለያዩ መንግስታዊ ለሆኑ ስራዎች G-I-V           18.00€   72.00 €
ለውጭ ባለሀብት ተቀጣሪ W-V           36.00€  54.00€   72.00 €
ለመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጣሪ G-V           27.00€ 36.00€ 54.00€
ለNGO N-V           54.00€
ለ አህጉራዊና አለምአቀፍ ድርጅት ተቀጣሪ R-I           45.00€ 63.00€ 81.00€
ለአጭር ስብሰባ ፣ለወርክ ሾፕ፣ለ አውደ ጥናት C-V           27.00€
ለሚዲያ ጋዜጠኞች J-V           36.00€
ለግል ድርጅት ተቀጣሪ P-E           27.00€ 45.00€ 72.00€

 

የትራንዚት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • ቪዛ ጠያቂው ኢትዮጵያን አቋርጦ ለማለፍ በራሱ ወይም በወኪሉ አማካኝነት ጥያቄ ሲያቀርብ 
 • ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ
 • የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ
 • በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ
የትራንዚት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር
ለ 12 ሰአት 21.50€
ለ 24 ሰአት 36.00€
ለ 48 ሰአት 45.00€
ለ 72 ሰአት 54.00

ለኤርትራዊያን የቱሪስት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • ቋሚ መኖሪያቸው በኤርትራ ውስጥ ለሆኑ ኤርትራዊያን ቅፅ አንድ እንዲሁም ከኤርትራ ውጭ ለሚኖሩ ትውልድ ኤርትራዊያን ለሆኑ አመልካቾች ቅፅ 2 ተሞልቶ ሲቀርብ
 • በተሞላው ቅፅ መሰረት  ተጨማሪ ማጣራት አድርጎ  ወደ በላይ አካል ከተላከ በኋላ ቪዛው ሲፈቀድ
 • የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ
 • የቱሪስት ቪዛ አገልግሎት ለመጠየቅ በቅድሚያ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ሲያሲዙ ብቻ ይስተናገዳሉ

ለኤርትራዊያን የሥራ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • የቪዛ አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ 1 በአግባቡ ተሞልቶ ሲቀርብ፣
 • የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ፣
 • ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ፣
 • አመልካቹን ኢትዮጵያ የሚጋብዘው ድርጅት አዲስ አበባ ኢሚግሬሽን ቀርቦ ለአመልካች የስራ ቪዛ ፈቃድ ጠይቆ ሲያገኝ
 • ለኢንቨስትመንት ስራ የሚሄዱ ከሆነ መኢንቨስትመንት መሄዳቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  አያይዘው ሲያቀርቡ፣
 • ለስራ ተቀጥረው የሚሄዱ ከሆነ የቀጣሪ ድርጅቱ ዝርዝር መረጃና ይድጋፍ ደብዳቤ እንዲሁም፣
 • የሚሲዮኑ የውሳኔ ሀሳብ ታክሎበት የበላይ አካል በሚወስነው መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፣

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b1%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5/%e1%8b%a8%e1%89%aa%e1%8b%9b-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8d%e1%89%b5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *