ከወንጀል ነጻ መሆንን ለማረጋገጥ አሻራ መቀበልና መላክ

ከወንጀል ነጻ መሆንን ለማረጋገጥ አሻራ መቀበልና መላክ አገልግሎት

*ጠቃሚ ማስታወሻ – ከወንጀል ነጻ መሆንን ለማረጋገጥ አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲያችን ከመምጣትዎ በፊት በ 01 47 83 27 42 ወይም 01 47 83 26 35 በመደወል ቀጠሮ መያዝ እንደሚያስፈልግ እናሳስባለን

 • አገልግሎት ጠያቂው በአካል ቀርቦ አሻራ ይሰጣል፣
 • በአካል መቅርብ የማይችሉ ተገልጋዮች የአሻራ ናሙና መቀበያ ቅጹን ከሚሲዮኑ ዌብ ሳይት ፕሪንት በማድረግና በአካባቢይቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም Nottary Office ቀርቦ አሻራ በመስጠት በሚኖሩበት አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጦ ወደ ኤምባሲው በፖስታ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡(ቅፁን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ)
 • በፖስታ ቤት በመላክ አገልግሎት የምትጠይቁ ባለጉዳዮች  የመላኪያውም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘትበተገልጋዮች መሟላትየሚገባቸውመስፈርቶች

 • አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይንም የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
 • በጀርባው ላይ ሙሉ ስም የተፃፈበት ሁለት የፓስፖርት ልክ ፎቶ ግራፍ  ማቅረብ/መላክ (ፎቶግራፉ  3X4 መጠን ያለው ሆኖ ሁለት ጆሮዎችን ፊት ለፊት የሚያሳይና መደቡ ነጭ መሆን ይኖርበታል፡፡
 • ጉዳዩን በአገር ቤት ተከታትሎ ለሚያስፈፀም  ሰው የተሰጠ የውክልና   ሰነድ፣ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)

የአገልግሎት ክፍያ

 •  ለኢትዮጵያዊያን እና ለትውልድ ኢትዮጵያውያን ሃምሳ ሰባት (57) ዩሮ፣
 •  ለውጭ ዜጎች ሰማንያ ሰባት (87 ) ዩሮ ፣
 • አገልግሎቱን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቱን በፖስታ ቤት በኩል ልከው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበትና  Tracking Number ያለው መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚገባ ሲሆን ክፍያውን ለኤምባሲው የተፃፈ፡-
 • የክፍያ ትዕዛዝ  /MONDANT CASH/ ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ በመላክ መክፈል ያስፈልጋል፡፡

 

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b1%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5/%e1%8a%a8%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%8d-%e1%8a%90%e1%8c%bb-%e1%88%98%e1%88%86%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8c%a5-%e1%8a%a0%e1%88%bb%e1%88%ab-%e1%88%98

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *