«

»

የኦሮሚያ ዳያስፖራ ፌስቲቫል,ከሀምሌ 27 – ነሀሴ 04 ቀን 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ

OROMIYA DIASPORA FESTIVAL R AMHARIC

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከሀምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ነሀሰ 04 ቀን 2007 ዓ.ም የክልሉን ዳያስፖራ ፌስቲቫል ለማክበር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የክልል የዳያስፖራ አባላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቲኬት ዋጋ ቅናሽ እንደሚያደርግ ገልፆልናል።

በመሆኑም በፌስቲቫሉ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የክልሉ የዳያስፖራ አባላት ቀጥሎ በተዘረዘረው የቲኬት ዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን የምትችሉ መሆኑን ለመግልፅ እንወዳለን።

የተደረገው የቲኬት ዋጋ ቅናሽ

  1. እ.ኤ.አ ከጁን 3 እስከ ጁን 30, 2015 እና እ.ኤ.አ ከጁላይ 29 እሰከ ኦገስት 3, 2015 ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊዎች የዳያስፖራ አባላት ብቻ 40% ቅናሽ የሚደረግ ይሆናል።
  2. ከላይ ከተጠቀሱት የጉዞ ቀናት ውጭ ለሚጓጓዙ የበዓሉ ተሳታፊ የዳያስፖራ አባላት ቲኬታቸውን እ.ኤ.አ ከጁን 21 እስከ 30, 2015 ባለው ጊዜ እስከገዙ እና ከአስር ባላነሰ አባላት በቡድን ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊ የዳያስፖራ አባላት የ15% ቅናሽ የሚደረግ ይሆናል።
  3. የሻንጣ መጠን 2PC/32 ኪሎ ለእያንዳንዱ መንገደኛ ነው።
  4. ማንኛውም መንገደኛ ከላይ የተጠቀሰውን ቅናሽ የሚያገኘው የአዘጋጁን የትብብር ደብዳቤ ሲያቀርብ ነው።
  5. ይህ የቅናሽ አገልግሎት የሚሰጠው ቲኬቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮዎች ሲገዛ ብቻ ነው።
  6. የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በበዓሉ ወቅት የመኝታ፣ የምግብ እና በአገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል።

For more information, please contact:

Mr. Berihun Degu, (Diaspora Affairs):
cell +33 61 03793 12 or +33 1 47 83 37 07: kurafima@gmail.com

Mr. Samuel Isa, (Public Affairs):
cell +33 6 19 42 41 50 or+33 1 47 83 37 10 : samre539@gmail.com.

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ  

ፓሪስ

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%8b%b3%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ab-%e1%8d%8c%e1%88%b5%e1%89%b2%e1%89%ab%e1%88%8d%e1%8a%a8%e1%88%80%e1%88%9d%e1%88%8c-27-%e1%8a%90%e1%88%80