«

»

የቀድሞው ፓስፖርት ከ November, 24 / 2015 በፊት ከአገልግሎት ውጪ ይሆናል

ዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ሙሉ በሙሉ Machine Readable ያልሆኑ ፓስፖርቶችን እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 24 ቀን 2015 በፊት ከአገልግሎት ውጪ ለማውጣት የሚፈልግ መሆኑን ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ አሳውቋል። በመሆኑም  የቀድሞ ማኑዋል ፓስፖርት የያዛችሁ የፈረንሳይ ፣ የስፔይን፣ የቱኒዚያ ፣ የፖርቹጋል እና የቫቲካን ነዋሪ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በስልክ ቁጥር: +33 147833628 / +33 147832268 በኤምባሲው የስራ ሰአት በመደወል ለኤምባሲያችን እንድታሳውቁ እያሳሰብን፤በተቻለ ፍጥነት ፓስፖርታችሁን እንድታስቀይሩ እንመክራለን :: ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የቀድሞ ማኑዋል የኢትዮጵያ ፓስፖርት ምስል ከዚህ በታች የተያያዘ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

  Old Passport

Permanent link to this article: http://ethiopianembassy.fr/%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%8b%b5%e1%88%9e%e1%8b%8d-%e1%8d%93%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8a%a8-november-24-2015-%e1%89%a0%e1%8d%8a%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d